መንግስት ሀገራችን ከነበረችበት ድህነትና ኋላቀርነት ለማላቀቅ የህብረተሰቡን የኢኮኖሚና ማህበራዊ የላቀ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ዘርፎችን እየለየና በሂደት ዘርፉን ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በመቅረጽና ወደ ተግባር በመግባት ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የበርካታ ዜጎችን የስራ አጥነት ችግር በመቅረፍ ኑሯቸው እንዲሻሻል እየተደረገ ይገኛል፡፡
የልደታ ክፍለ ከተማ አገራችን ኢትዮጵያ የበለጸገችና መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ በማሰለፍ የህዝቧን የኑሮ ሁኔታ ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሻሻል የሚያስችል መዋቅራዊ አደረጃጀት በመፍጠር ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ሀገራዊ የድህነት ቅነሳ ግብን ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ከሚገኙ ክፍለ ከተሞች ላይ ትገኛለች፡፡
የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የዘርፉን አዲስ የልማት ስትራቴጂ ማጽደቅ ተከትሎ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ በስትራቴጂው የተቀመጡ ተልዕኮዎችን ለመወጣት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ጽ/ቤቱ በተዋቀረው በእያንዳንዱ የስራ ሂደት መደባዉን ሳይጠብቅ አሁን ባለዉ አደረጃጀት ሊተገበሩ የሚገባቸውን ተግባራት ከከተማው መሪ እቅድና ከዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በመነሳት ዝርዝር እቅዶችን በማውጣት እየተገበረ ይገኛል፡፡
ጽ/ቤቱ ለተገልጋዮች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻልና ለማቀላጠፍ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም ተገልጋዮች ወደ ጽ/ቤቱ አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡ የሚሰጣቸውን የአገልግሎት ዓይነትና ጥራት፤ የሚወስደውን ጊዜ አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጋቸው ወጪና እንዲሁም በእነርሱ በኩል ማሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን ያመላከተ የተገልጋዮች ቻርተር ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡