በልደታ ክፍለ ከተማ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት

ለስራ እድል ፈጠራ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋት፣ በክ/ከተማችን የተንሰራፋውን ድህነትና ስራ አጥነትን ለመቅረፍ እና የዜጎችን እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስትራቴጂ በመቅረጽ ወደ ተግባር ገብቷል፡፡ በዚህም በ2015 በጀት አመት ባለፉት ወራት በተደረገ ርብርብ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

ይሁንና ለስራ ፈላጊ ዜጎች የሚያስፈልጓቸውን ድጋፎች በማመቻቸት የስራ እድል ፈጠራ ስራው ውጤታማ ቢሆንም በዘርፉ በከፍተኛ ቁጥር እያደገ የመጣውን የዜጎች የስራ ዕድል ይፈጠርልኝ ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋት፣ ማሻሻል እና በውጤታማነት መምራት አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት መንግስታዊ ድጋፎችን እና አገልግሎቶችን በተቀናጀ መልኩ በቁርጠኝነት አጠናክሮ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

አፈጻፀም

በልደታ ክፍለ ከተማ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት እስከዚህ ወር የተፈጠረ የስራ እድል ፣ ከተፈጠረዉ የስራ እድል የሴቶች ድርሻ ፣ የወጣቶች ድርሻና በቋሚነት የተፈጠረ የስራ እድል...

31,110(እቅድ ክንዉን 98.4% )

በክ/ከተማዉ እስከዚህ ወር የተፈጠረ የስራ እድል

14,610(46.9%)

ከተፈጠረዉ የስራ እድል የሴቶች ድርሻ

25,747 (82.7%)

ከተፈጠረዉ የስራ እድል የወጣቶች ድርሻ

27,825(89.4%)

በቋሚነት የተፈጠረ የስራ እድል

ጠቃሚ ሰነዶች

የሥራ ዕድል ፈጠራ መርሆዎች ፣ የስራ ፈላጊዎች ልየታ፣ አመዘጋገብ እና የግንዛቤ ፈጠራ ፣ በስራ ፈላጊነት ለመመዝገብ የሚጠየቁ መስፈርቶች ፣ የአጫጭር የስራ አመራር እና ክህሎት ስልጠና ፣ የስራ ዕድል ፈጠራ መንገዶች ፣ የንግድ ሕጉ የሚያቅፋቸው የአደረጃጀት ዓይነቶች ፣ ….

Download