ስራ ፈላጊ ®

የል/ክ/ከ/የስ/ኢ/ኢ/ል/ጽ/ቤት መጽሄት

ግንቦት 21, 2014

ቅጽ 1



በልደታ ክ/ከተማ

ባለፉት 9 ወራቶች ለ30 ሺ 879 ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል፡፡


ኢንተርፕራይዞቻችን እና የገበያ ትስስር



የጽ/ቤቱ ኀላፊ መልእክት


እንዴት የስራ ፈላጊዎችን ቁጥር መቀነስ ይቻላል?

መልካም ተሞክሮዎች

home

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 
የልደታ ክፍለ ከተማ

የስ/ኢ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ኀላፊ መልእክት

የክ/ከተማችንን ነዋሪዎች ተሳትፎ በማሳደግ የስራ አጥነት ችግር እና የድህነት መጠንን በመቀነስ የህዝቡን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ የተግባር ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስቱሪ ልማት ጽ/ቤት በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት የተገልጋዮችን እርካታ በማሻሻል ለከተማው ዕድገት የድርሻውን እንዲያበረክት እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ እየሠራ ይገኛል፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ የበለጸገችና መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ በማሰለፍ የህዝቧን የኑሮ ሁኔታ ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሻሻል የሚያስችል መዋቅራዊ አደረጃጀት በመፍጠር ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ሀገራዊ የድህነት ቅነሳ ግብን ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡ በክ/ከተማችን የአስተዳደሩን ትኩረት የሚሹ እና በተደራጀ የልማት እና መልካም አስተዳዳር ዕቅድ ምላሽን የሚጠይቁ በርካታ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች በመኖራቸውና የጥቃቅን ፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ለኢኮኖሚያዊ ፣ለማህበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት በተለይ ለኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ትግበራ መሳካት ያለውን ፋይዳ ግምት ውስጥ በማስገባት ከመቸውም ጊዜ በላይ በበቂ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ዝግጅት ወደ ትግበራ ገብተናል፡፡

በቀጣይ 2 ወራት የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል ተባለ፡፡

Lidetapress May 10, 2022

የወጣቶችን የስራ እድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የ60 ቀናት እቅድ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱንም አቶ አስፋው ተናግረዋል። የጽ/ቤቱ ም/ኃላፊ አቶ ሀሰን ጀማል በበኩላቸው ለወጣቱ የሚሆኑ የተለያዩ የስራ ዕድሎችን በማመቻቸት በማሰልጠንና ወደ ስራ በማስገባት የወጣቱን ወቅታዊ ጥያቄ የመመለስ ስራ አየተሰራ ነው ብለዋል።

በቀጣይ 2 ወራት በስራ እድል ፈጠራው ዘርፍ የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የልደታ ክ/ከ/የስ/ኢ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ገለፀ። ጽ/ቤቱ ከወጣት ማህበራት ጋራ በመሆን ወጣቶች ወደ ስራ እንዲሰማሩ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ አከናውኗል። የልደታ ክ/ከተማ ም/ስራ አስፈፃሚና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስቱሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስፋው ፋራ እንደተናገሩት ወጣቶችን በተለያዩ የስራ ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑና የኢኮኖሚ

ችግር እንዳይኖርባቸው በሚያስችል መልኩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል ።

የወጣቶች ማህበር ም/ሰብሳቢ ወጣት ጎይቶም አረጋይ በበኩሉ ጽ/ቤቱ የወጣቱን ችግር በመረዳት ከማህበሩ ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ወጣቱ በተሰጠው እድል መጠቀም አለበት ብለዋል። የምክክሩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ስራ አጥነት በተደጋጋሚ የሚያነሱት ጥያቄ በመሆኑ በሚሰጠው የስራ ዕድል እንደሚጠቀሙ ተናግረዋል።

በልደታ ክ/ከተማ ባለፉት 9 ወራቶች ለ30 ሺ 879 ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል ተባለ።

Lidetapress April 14, 2022

በልደታ ክ/ከተማ ባለፉት 9 ወራቶች ለ30 ሺ 879 ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል ተባለ። የክ/ከተማው የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የ9 ወራት አፈፃፀሙን ገምግሟል።

4

የ9 ወራት አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ

የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ሀሰን ጀማል በግምገማው ወቅት እንደተናገሩት ባለፉት 9 ወራቶች የወጣቶችንና የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የስራ አማራጮችን ለይተን ለተግባሩ ስኬት ባደረግነው ርብርብ ለ30 ሺ 879 ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ችለናል ብለዋል።

በስራ እድል ፈጠራው 19 ሺ 972 ወጣቶችንና 14 ሺ 184 ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ሲሉም አቶ ሀሰን ገልፀዋል። በ9 ወራቶች ለ23 ሺ 447 ዜጎች ቋሚ ለ7ሺ 434 ጊዚያዊ የስራ እድል መፈጠሩንም ተገልጿል።

በቀጣይነትም በበጀት ዓመቱ የተያዙ ግቦችና ፕሮግራሞች ለማሳካት የአመለካከት፣ የክህሎት እንዲሁም የግብአት ክፍተቶችን በማሟላት የዘርፉን የማስፈፀም አቅም መገንባት በትኩረት ይሰራበታል፡፡ እንዲሁም የክ/ከተማችንን ነዋሪዎች ተሳትፎ በማሳደግ የስራ አጥነት ችግር እና የድህነት መጠንን በመቀነስ የህዝቡን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ የተግባር ስራ ይሰራል፡፡

 a  1

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ለአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ አስተባባሪዎች ያዘጋጀው የጋራ ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሄደ።

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ስራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ በባህር ዳር ከተማ በሁለተኛ ዙር ከአማራ፣ ሲዳማ፣ አፋር፣ ሶማሌ ፣ ቤኒሻንጉል ብሔራዊ ክልሎች እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ለተውጣጡ አስተባባሪዎች ያዘጋጀው የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ነዉ። የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አደረጃጀት እና ተልዕኮ፣ እየተሻሻለ በሚገኘው የዘርፉ ስትራቴጂ እና መመሪያዎች ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ አፈፃፀም መመሪያ እና የቤተሰብ ንግድ አደረጃጀት፣ ማህበራዊ ስራ ፈጣሪነት፣ በአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያጋጠሙ ችግሮች እና የመፍትሔ አቅጣጫዎች እንዲሁም የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት እና የማዕከላቱ ሪፖርት ቅብብሎሽ ገለፃ ተደርጎ ውይይት የተካሄደባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው። ተሳታፊዎቹ በውይይቱ ካነሷቸው ችግሮች መካከል በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና በጣቢያዎቹ መካከል ያሉ መዋቅሮች እና የተለያየ አሰራር መኖርን፣ የበጀት እና ሎጂስቲክ እጥረት፣

የሼድ ፣ የብድር አቅርቦት እና አመላለስ ችግሮች ይገኙባቸዋል። ለጥያቄና አስተያየቶቹ ምላሽ የሰጡት የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን ከጣቢያዎቹ ጋር አብረን ካልሰራን የሥራ ፈጠራ ሥራ ተሠርቷል ማለት አንችልም በማለት መድረኩ ከሞላ ጎደል በዘርፉ ያሉ ችግሮች የተነሱበት መሆኑን የተናገሩ ሲሆን የመጀመሪያ እንደመሆኑ የተነሱትን ጥያቄና አስተያየቶች በመያዝ የአቅም ግንባታ እና ልምድ ልውውጥ ሥራዎችን አቅዶ መሥራት እና ተገቢ መሆኑን አንስተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በልደታ ክ/ከተማ በመገኘት አገልግሎት አሰጣጡን ተመለከቱ ።

Lidetapress June 2, 2022

ከንቲባዋ በጉብኝታቸው ወቅት እንደተናገሩት አገልግሎት አሰጣጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ነው ብለዋል። ሁሉንም ችግሮች በአንዴ መፍታት ባይቻልም ለአንገብጋቢ ችግሮች ቅድሚያ እየሰጠን እየፈታን እንሄዳለን ሲሉም ከንቲባዋ ተናግረዋል። የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰግደው ሀ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው የማህበረሰባችንን ችግሮች ደረጃ በደረጃ እየፈታን መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን እንሰራለን ብለዋል።

በተያያዘ ዜና ከንቲባዋ በልደታ ክ/ከተማ በመንግስት ተቋማትና በግለሰቦች ቅጥር ግቢ ውስጥ እየተተገበረ ያለውን የጓሮ አትክልት ልማት ጎበኝተዋል። ከንቲባዋ በመስክ ምልከታው ወቅት እንደተናገሩት በተቋማትና በግለሰቦች መኖሪያ ቤት ያሉ ክፍት ቦታዎችን በአጭር ጊዜ በሚደርሱ የጓሮ አትክልቶች ለመሸፈን እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ውጤት እያመጣ ነው ብለው ተግባሩ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች

የኑሮ እፎይታን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና ስላለው ወደ ሌሎች ቦታዎችም ማስፋት ያስፈልጋል ብለዋል። የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰግደው ሀ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው የጓሮ አትክልት ልማትን በተቋማትና በግለሰቦች ቤት ባሉ ክፍት ቦታዎች በመተግበር በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ችለናል ብለው ልማቱ ከዚህ በበለጠ ስኬታማ ሁኖ ወደ ሌሎች ቦታዎች እንዲሰፋ ጠንክረን እየሰራን ነው ብለዋል።

የስራ እድል ፈጠራና  የስራ አጥነት ችግር

2

አገራችን ኢትዮጵያ የበለጸገችና መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ በማሰለፍ የህዝቧን የኑሮ ሁኔታ ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሻሻል የሚያስችል መዋቅራዊ አደረጃጀት በመፍጠር ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ሀገራዊ የድህነት ቅነሳ ግብን ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡

የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስቱሪ ልማት ጽ/ቤት የተሰጠውን ስልጣንና እና ኃላፊነት እንዲያሳካ ፖሊሲዎችን፣ ህጐችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በስፋት በማስተዋወቅና በማስፈፀም፣ ኅብረተሰቡን በማሳተፍ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ድጋፍ በማቀናጀት በክ/ከተማችን የሚታየውን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ የሥራ ሥምሪት አገልግሎት በማስፋፋት የሥራ ዕድል እንዲፈጠር በማድረግ ህጋዊ፣ ፍትሃዊና ተደራሽ የዜጎች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በሚያስችል ሁኔታ ወደ ተግባር በመግባት ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የበርካታ ዜጎችን የስራ አጥነት ችግር በመቅረፍ ኑሯቸው እንዲሻሻል እየተደረገ ይገኛል፡፡

l 4

እንዴት የስራ ፈላጊዎችን

ቁጥር መቀነስ ይቻላል?

በክ/ከተማችን የሚታየውን ድህነትና ስራ አጥነት ለመቀነስ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች በምግብ ዋስትና ተጠቃሚ በማድረግ ኑሮአቸውን በማሻሻል፣ በኢንተርፕራይዝ በማደራጀትና በማልማት፣ኢንዱስትሪ ልማት በማስፋፋትና በማበልጸግ የኢንዲስትሪ መር ኢኮኖሚ ሽግግር በማረጋገጥ፣ መንግስታዊ ድጋፎችን በመስጠት፣ በውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ፣ አምራች ዜጎችን ጤንነታቸውንና ደህንነት በማስጠበቅ፣የስራ ቦታና የስራ አከባቢዎችን ምቹ የስራ ሁኔታ በማረጋገጥ ፣ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ በማድረግ ለበርካታ የክ/ከተማችን ነዋሪዎች የስራ እድል መፍጠርና ኑሮ ማሻሻል ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ላይ ትኩረት በማድረግ በአዳማ የተካሄደው መድረክ ተጠናቀቀ፡፡

LS Minister May 06, 2022

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ አስተባባሪዎች እና የቢሮ ኃላፊዎች ጋር በአዳማ ከተማ ያካሄደውን መድረክ አጠናቋል።

ለመጀመሪያው ዙር ከሰባት ክልሎች ተወክለው የመጡት የጣቢያዎቹ አስተባባሪ እና ኃላፊዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት ጣቢያዎቹ ላይ የሚደርስ ጉዳት፣ የቁሳቁስ አለመሟላት፣ የስልጠናዎች አለመመቻቸት፣ የሠራተኞች ፍልሰት፣ ለዘርፉ የሚሰጠው ትኩረት ማነስ እና የመሳሰሉትን እንደችግር አንስተዋል።

ውይይቱን የመሩት የሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን መድረኩ ለሥራ ፈላጊው ወጣት ሥራ ለመፍጠር የሚሰሩት ጣቢያዎች ያሉባቸውን ችግሮች ለመረዳት ዕድል ሰጥቷል ብለዋል። ይህንንም ለመፍታት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና በጣቢያዎቹ መካከል ካሉት የክልል፣ የዞን እና የወረዳ አደረጃጀቶች ጋር ተመካክሮ የመፍተሔ አቅጣጫ የማስቀመጥ ድርሻውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደሚወጣ ተናግረዋል።

የመንገድ ላይ ባዛርና ኢግዚቢሽን አገልግሎት በአዲስ አበባ

የስ/ኢ/ኢ/ል/ቢሮ April 18, 2022

በስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የኢንተርፕራይዝ ድጋፍ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሀ ጥበቡ፣ የኮልፊ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል ረዲ፣ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ተጫነ አዱኛ እና ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በኮልፌ ክፍለ ከተማ ጦር ሀይሎች አደባባይ የመንገድ ላይ ባዛርና ኢግዚቢሽን በይፋ ተጀመረ።

ከውጭ የምናስገባውን የፍጆታ ምርት በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት የውጭ ምንዛሪን ለማስቀረት እና የኢንተርፕራይዞችን ምርት ጥራትና ብዛት ለሸማቾች በማስተዋወቅ የሀገር ውስጥ ፍጆታዎችን በሀገር በቀል ምርት ለመሸፈን ታሳቢ ያደረገ የመንገድ ላይ ባዛርና ኢግዚቢሽን መሆኑን የኢንተርፕራይዝ ድጋፍ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሀ ጥበቡ ተናግረዋል።

ከ58 በላይ ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን ወደ ወጪ እንደሚልኩ አቶ ፍስሀ ጠቁመዋል፡፡

ኢትዪጵያ ታምርት በሚል መሪ ቃል ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክርና የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ

የስ/ኢ/ኢ/ል/ቢሮ May 1, 2022

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣ ምክትል ከንቲባ እና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ምንስትር ክቡር አቶ መላኩ አለበል እና ሌሎች የፌደራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የአምራች እንደስትሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ጎብኝተዉ የምክክር መድረክም አከናዉነዋል፡፡

በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የኢንደስትሪ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይዘዲን ሙስባህ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በተመለከ የዉይይት ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ኢንደስትሪዎች የገቢ ምርት በመተካት፣የውጭ ምንዛሪ በማስገት፣ የስራ ዕድል በመፍጠር፣የፍጆታ ዕቃዎችን በማምረት በከተማው የማይናቅ ሚና እንዳላቸዉ በዉይይቱ ቀርቧል፡፡

በዉይይቱም በ2014 ዓ.ም ካለዉ 10,504 ኢንደስትሪዎች በጥራትና በቁጥር በማሳደግ በ2022 ዓ.ም 26,260 ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ምክትል ከንቲባ እና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገጸዋል፡፡በተጨማሪም አምራች ኢንደስትሪዎችን ምራታማነት ለማሳደግ በኢንቨስትመንት፣ በሽግግር፣የማምረቻ ቦታና የፋይናንስ ድጋፍ ሲደረግ እንደነበር ገልጸዉ አሁንም ተጨማሪ ጥረት ይጠይቃል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የአንድ ማዕከል አገልግሎት ጣቢያዎች ተሰሚ እንድንሆን የማድረግ ተልዕኮ አላቸው ተባለ፡፡

LS Minister May 05, 2022

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ስራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ለክልል እና ከተማ አስተዳደር የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ አስተባባሪዎች እና የቢሮ ኃላፊዎች የጋራ ግንዛቤ መፍጠሪያ አገር አቀፍ መድረክ ማካሄድ ጀምሯል።

መድረኩን ሲከፍቱ አያቶቻችን ያጎናፀፉንን ነፃነት ስናስብ ለልጆቻችን የምናወርሰው ታሪክ ሰርተን መሆን አለበት ያሉት የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ከቀበሌ ጀምሮ በሚሰጡት አገልግሎት ፖሊሲና ህጎችን ወደ ተግባር የሚቀይሩ በመሆናቸው ድህነትን በመቀነስ ኢትዮጵያውያን በብልፅግናችን ተሰሚ እንድንሆን ለማድረግ ትልቅ ተልዕኮ አላቸው ብለዋል።

ለአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ አስተባባሪዎች እና የቢሮ ኃላፊዎቹ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አደረጃጀት እና ተልዕኮን በተመለከተ እንዲሁም እየተሻሻለ በሚገኘው የዘርፉ ስትራቴጂ እና መመሪያዎች ላይ ገለፃ ተደርጓል። የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከ 2 ሺህ 100 በላይ ለሚሆኑ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰጪ ሙያተኞችና አመራሮች አቅም የመገንባት ስራ እያከናወነ ይገኛል።

የጣቢያዎቹ ሠራተኞች ዜጎችን ወደሥራ እንዲመጡ ከማንቃት ጀምሮ በሚሰጡ አገልግሎቶች ተስፋ እንዲሰንቁ በማድረግ ለሌሎች ብርሃን የሚሰጡ፤ ሚናቸው የላቀ መሆኑንም ገልፀዋል። ዘላቂ ነፃነትን የሚያረጋግጠው የኢኮኖሚ ነፃነት መሆኑን አፅንኦት የሰጡት ክብርት ሙፈሪሃት ለዚህም ጠቃሚ የሆነው የሥራ ባህል የሚገነባባቸውን ማዕከላት ክህሎት በመስጠት ወጣቶች አቅማቸውን እንዲጠቀሙ እንዲያደርጉ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

May Day የአለም የሰራተኞች ቀን

በኢትዮጵያ ተከበረ

የሰራተኞች መደራጀት ለአሰራራችን በተለይ ለአሰሪዎች ወሳኝ ነዉ ተባለ፡፡

አለማቀፍ የሰራተኞች ቀን (ሜይ ዴይ) በዓለም 133ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ47ኛ ጊዜ የሰራተኞች መደራጀት ለሰላም፣ለምርታማነት፣ለኑሮ መሻሻል በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ ተከበረ፡፡ በበዓሉ ላይ የስራና ክህሎት ምኒስቴር ምንስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚልን ጨምሮ ሌሎች የፈደራል እኛ የከተማ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የሰራተኞች መደራጀት ለአሰራራችን በተለይ ለአሰሪዎች ወሳኝ በመሆኑ አሰሪዎች ከዛሬ ጀምራችሁ የሰራተኞችን መደራጀት እንድትደግፉ ሲሉ የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፊደሬሽን ፕሮዝዳንት አቶ ታደለ ይመር ገለጹ፡፡ አቶ ታደለ ይመር ገለጹ አያይዘዉም የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌድሬሽን የኢትዮጵያ ሰራተኞችን ክብር የሚያስጠብቅና የሚያስከብር ነዉ ብለዋል፡፡

የአለም የሰራተኞች ቀን መከበር ዋና አላማዉ ለሰራተኞች መብትና ጥቅም መከበር መስዋዕት የሆኑ ቀደምት ሰራተኞች በመዘከር ለቀጣይ የሰራተኛዉ ትግል አንድነት ቃል ኪዳን ለማደስ ነዉ ሲሉ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁ ፎሎ ገልጸዋል፡፡

አቶ ካሳሁን አያይዘዉም የሰራተኞች መደራጀትን በሚመለከት በኢትዮጵያ ህገመንግስት ኢትዮጵያ ተቀብላ ባጸደቀችዉ የአለም ስራ ድርጅት ኮንቬንሽን ቁጥር 87 እና 98 መሰረት በነጻ የመደራጀት መብት የተደነገገ ቢሆንም እስካሁን በአብዛኛዉ አሰሪዎችና በአንዳንድ አስፈጻሚዎች በኩል እየተጣሰ መሆኑን ገልዋል፡፡

ኢንተርፕራይዞቻችንና  የገበያ ትስስር

2 l 4

የጥቃቅን ፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ለኢኮኖሚያዊ ፣ለማህበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት በተለይ ለኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ትግበራ መሳካት ያለውን ፋይዳ ግምት ውስጥ በማስገባት የዘርፉን ዕድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትኩረት በመስጠት እየሰራ ይገኛል።
በዘርፍ ተደራጅተው ለሚሰሩ አንቀሳቃሾች ምርትና ምርታማነታቸውን ማሳደግ የሚያስችሉ መንግስታዊ ድጋፎችን በመስጠት በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ገበያውንም የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ባለፈው በጀት ዓመት በክ/ከተማችን ተደራጅተው የገበያ ትስስር የሚፈልጉ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የገበያ ትስስር ሊፈጠርባቸው የሚችሉ መስኮችን በመለየት የገበያ ትስስር ስራ ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ኢንተርፕራይዞች በገበያ ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲወጡና ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ በገበያ ትስስር ተጠቃሚ በማድረግ በኩል ባሳለፍነው ወራት ውስጥ የተለያዩ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡

የኢንተርፕራይዞች ዉጤታማነት

ለሀገር እድገት መሰረት ነዉ፡፡

በዚህም መሠረት በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ በሀገር ውስጥ ገበያ ለ708 ኢንተርፕራይዞች የብር 233,725,090.63 የገበያ ትስስር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ታቅዶ ለ999 (>100%) ኢንተርፕራይዞች የብር 229,152,728.48 (98%) የገበያ ትስስር ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ በዉጪ የገበያ ትስስር ለ3 ኢንተርፕራይዞች የብር 1,459,440 የገበያ ትስስር ለመፍጠር ታቅዶ ለ3 (100%) ኢንተርፕራይዞች የብር 4,934,000 (>100%) የገበያ ትስስር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በሀገር ውስጥ ገበያ ትስስር ባሳለፍነው ዘጠኝ ወራት የተሻለ አፈፃፀም ቢኖርም በኢንተርፕራይዝ ለታቀፉ አንቀሳቃሾች በሸማች ማህበራት እንዲተሳሰሩ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በቀጣይ በቂ ትኩረት ልሰጠዉ ይገባል፡፡

አዘጋጅ፡- ማርቆስ ሙላት