ስራ እድል ®

የል/ክ/ከ/የስ/ኢ/ኢ/ል/ጽ/ቤት መጽሄት

ሚያዝያ 28, 2015

ቅጽ 2



በልደታ ክ/ከተማ

ባለፉት 10 ወራቶች ለ31 ሺ 950 ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል፡፡


ኢንተርፕራይዞቻችን እና የገበያ ትስስር



የጽ/ቤቱ ኀላፊ መልእክት


እንዴት የስራ ፈላጊዎችን ቁጥር መቀነስ ይቻላል?

መልካም ተሞክሮዎች

home

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 
የልደታ ክፍለ ከተማ

የስ/ኢ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ኀላፊ መልእክት

የክ/ከተማችንን ነዋሪዎች ተሳትፎ በማሳደግ የስራ አጥነት ችግር እና የድህነት መጠንን በመቀነስ የህዝቡን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ የተግባር ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስቱሪ ልማት ጽ/ቤት በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት የተገልጋዮችን እርካታ በማሻሻል ለከተማው ዕድገት የድርሻውን እንዲያበረክት እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ እየሠራ ይገኛል፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ የበለጸገችና መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ በማሰለፍ የህዝቧን የኑሮ ሁኔታ ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሻሻል የሚያስችል መዋቅራዊ አደረጃጀት በመፍጠር ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ሀገራዊ የድህነት ቅነሳ ግብን ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡ በክ/ከተማችን የአስተዳደሩን ትኩረት የሚሹ እና በተደራጀ የልማት እና መልካም አስተዳዳር ዕቅድ ምላሽን የሚጠይቁ በርካታ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች በመኖራቸውና የጥቃቅን ፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ለኢኮኖሚያዊ ፣ለማህበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት በተለይ ለኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ትግበራ መሳካት ያለውን ፋይዳ ግምት ውስጥ በማስገባት ከመቸውም ጊዜ በላይ በበቂ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ዝግጅት ወደ ትግበራ ገብተናል፡፡

ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከወንዝ ዳርቻና በልማት ለተነሱ የመኖሪያ ቤት አስተላለፉ።

Lidetapress መጋቢት 26, 2015

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ባስተላለፍት መልዕክት ከወንዝ ዳርቻና በልማት ምክንያት ለተነሱ ዜጎች በግልፅኝነትና ፍትሀዊነት የሚገባቸውን የመኖሪያ ቤት፣ የመሬትና የካሳ ክፍያ ሰጥተናል ፥አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ውብ፣ ምቹና አረንጓዴ ለማድረግ የጀመርነውን ጥረት የከተማችን ነዋሪዎች ማገዝ ይኖርባቸዋል ብለው ከተማችን ስትለማ ከማንም በላይ ተጠቃሚው ነዋሪዎቿ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

4

ከንቲባዋ አክለውም ዛሬ የእድሉ ተጠቃሚ የሆኑ በወንዝ ዳርቻ ይኖሩ የነበሩ ዜጎች በተበከለ ፍሳሽ ምክንያት ለጤና ችግር ብሎም ክረምት በመጣ ቁጥር ለጎርፍ አደጋ ስጋት ተጋላጭ ነበሩ ያሉ ሲሆን እነሱን አንስተን ደረጃውን በጠበቀ ምቹ የመኖሪያ ቤት እንዲኖሩ ከማድረግ ባለፈ ወንዞችን በማከም፣ በማፅዳትና በማስዋብ የወንዝ ዳር መዝናኛዎችን እየገነባን የቱሪስት መስህብ እና የገቢ ምንጭ እንዲሆኑ እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል።

የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰይድ ዓሊ እንደተናገሩት የከተማችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ፤ለአብነትም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚኖሩ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የ60/90 ቀናት ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን መጥቀስ ይቻላል ብለው በ60/90 ቀናት ፕሮጀክቶች የበርካታ ነዋሪዎችን ህይወት መቀየር ተችሏል ሲሉ ገልፀዋል።

በክፍለ ከተማችን ለመኖሪያ ምቹ ያልሆኑ መንደሮች፣ሰፈሮችና አካባቢዎች መኖራቸውን የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚው ሰው ተኮር ስራዎቻችንን በማጠናከርና መንደሮችን መልሰን በመገንባት ውብና ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች ልደታን እንፈጥራለን ብለዋል።

 a  1

የልደታ ክ/ከተማ አመራሮች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች ማዕድ አጋሩ።

Lidetapress መጋቢት 25, 2015

የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች የትንሳኤና የረመዳን በዓል ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ነዋሪዎች ማዕድ አጋርተዋል።

4

ከወዲሁ መልካም የትንሳኤ እና የሮመዳን በዓል ይሁንላችሁ!!

በማዕድ ማጋራቱ መልዕክት ያስተላለፍት የክ/ከተማው ምክትል ስራ አስፈጻሚና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሐኑ ኤኬታ እንደተናገሩት መጪውን የትንሣኤና የረመዳን በዓል ምክንያት በማድረግ የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች በራሳቸው ተነሳሽነት ከኪሳቸው በማዋጣት ማዕዱን ማጋራታቸው የአንድነት ፣የአብሮነትና የመቻቻል መገለጫ መሆኑን ጠቁመው ይህን ያስተባበሩ አካላትንም አመስግነዋል።

የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባዬ ባይሌ በበኩላቸው ሁለቱን በዓላት ምክንያት በማድረግ አመራሮች የመረዳዳትና የአብሮነት መገለጫ በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ነዋሪዎች ማዕድ አጋርተናል ብለዋል።

 a  1

'ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችንን ተባብረን ለስኬት እናበቃለን' የልደታ ክፍለ ከተማ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት።

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የግንባታ ፕሮጀክት የመሰረተ- ድንጋይ የተጣለበትን 12ኛ ዓመት ክብረ በዓል መነሻ በማድረግ የህዝብ ንቅናቄ እና የገቢ አሰባሰብ መርሀ ግብር አስጀምሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ምንዳዬ ክብረ በዓሉን መነሻ አድርገው እንደገለፁት ግድቡ 90% ማጠናቀቅ የተቻለ ሲሆን ቀሪውን 10% ለማጠናቀቅ 60 ቢሊዮን የሚያስፈልግ ሲሆን እንደዐይን ብሌን የምናየው የባንዲራ ፕሮጀክታችን የሆነው ህዳሴ ግድብን በማይለወጥ መርህ ጸንተን ጠላትንም አሳፍረን የእናት አባቶቻችን አደራ መወጣትና ሀገራችን ከድህነት ማላቀቅ ይኖርብናል ብለው ለታለመው ዓላማ መሳካት የአመራሩ ቁርጠኛ መሆንና የተለያዩ ዘዴዎችንም ተጠቅሞ ሀብት ማሰባሰብና ግድቡ እንዲጠናቀቅ ጥረት ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል። አቶ ዳዊት አክለውም ልደታ ክፍለ ከተማ ከዚህ ቀደም በሀብት ማሰባሰብ ላይ ሰፊ ርብርብ አድርጎ ዛሬ ላይ ለተደረሰው ውጤት የማይረሳ የትውልድ አሻራ ማሳረፍ ችሏል ለቀሪው 10% ከታቀደው በላይ ሀብት በማሰባሰብ ከበፊቱ በተሻለ መንገድ በመገኘት አስመስጋኝ ውጤት ታመጣላቹ የሚል ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይድ አሊ በበኩላቸው እናት አባቶቻችን ደም ያፈሰሱላት ዋጋም የከፈሉላት ሀገራችን ዛሬም እንደቀደምት ጊዜያት አደራቸውን ሰጥተውን ለትውልድ የሚተላለፍ ትልቅ ቅርሳችን ሀብታችን የሆነውን ታላቁ ህዳሴ ግድባችንን አጠናቀን አደራችንን መወጣት እንዳለብንም ያስታውሱናል ያሉት አቶ ሰይድ ግድቡ ሙሉ መጠናቀቅ እንዲችል አንዱ መፍትሄ ባለሀብቱን ህብረተሰብ፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ግብር የማይከፍለውን በማስከፈል፣አገልግሎታችንን በማዘመን፣ ት/ት ተቋማት፣የመንግስት ሰራተኞችንና ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀምና ተሳታፊ በማድረግ ከተማ አስተዳደሩ በሰጠው አቅጣጫ መሰረት ውጤት ማስመዝገብ ይኖርብናል ብለዋል።

የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሀኑ ኤኬታ ግድቡ የእያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን ግዴታና ኃላፊነት በመሆኑ የሚጠበቅብንን በመወጣት በድህነትና በርሀብ የምትነሳውን ሀገራችንን ወደ እድገት እንድታቀና አንድነታችንን በማጠናከር የዜግነት ግዴታችንን መወጣት ብሎም ጥረታችንም ውጤታማ አድርገን ሀብት በማሰባሰቡም ረገድ ሙሉ ተሳታፊዎች መሆንና ህዳሴውን ሙሉ ለሙሉ ተገድቦ እንዲጠናቀቅ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል። በመጨረሻም የህዳሴ ግድብ 12ኛ አመት ክብረ በዓልን መነሻ ያደረገ ሰነድ ማቅረብና 8100 ላይም አጭር መልዕክት መላክ የተቻለ ሲሆን ሀብት ለማሰባሰብ ወረዳ 08 የመጀመሪያው ሆኖ ዋንጫውን ተረክቧል።

አምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርቶችን በማምረት በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ልሆኑ ይገባል ተባለ፡፡

Lidetapress መጋቢት 15, 2015

አምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርቶችን በማምረትና በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ሆነው በመቅረብ በኢኮኖሚ እድገት ላይ አስተዋፆ ሊያደርጉ ይገባል ሲል የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገለፀ። በአስተዳደሩ " ኢትዮጲያ ታምርት " በሚል መሪ ቃል ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ ንግግር ያደረጉት የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰይድ ዓሊ እንደተናገሩት አምራች ኢንዱስትሪዎች ያለንን ፀጋ ተጠቅማቹህ ጥራት ያላቸው ተኪ ምርቶች በማምረት በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ልትሆኑ ይገባል ብለው ድህነትንና ኃላ ቀርነትን ለማሸነፍ የእናንተ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋልና በህብረት በርትታቹህ መክራት ይኖርባቹሃል ሲሉ ተናግረዋል። አምራች ኢንዱስትሪዎች ሰርታቹህ፣ ያላቹህን እውቀት አጎልብታቹህና ቴክኖሎጆን ተጠቅማቹህ ለውጥ በማምጣትና አቅም በመፍጠር ሽግግር ማድረግ ይገባቹሃል ያሉት ስራ አስፈፃሚው በመተባበርና በመደጋገፍ ሰርተን የኢኮኖሚ ጥገኝነታችንን ከቀየርን ኢትዮጲያ ታድጋለች ትበለፅጋለች ብለዋል።

የክ/ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሀኑ ኤኬታ በበኩላቸው የመስሪያ ቦታዎችን ህጋዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ይገባል ፤ 5 ዓመት የሞላው ተጠቃሚ ለተተኪ የስራ እድል ተጠቃሚዎች መልቀቅ ይኖርበታል ብለው ለማደግና ለመለወጥ እኔ ብቻ ከሚል አስተሳሰብ ወጥተን መስሪያ ቦታዎችን ለተተኪዎች በመልቀቅና ተጋግዘን በመስራት መለወጥ አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢዘዲን ሙስብሀ በበኩላቸው መንግስት የመስሪያ ቦታዎችን ለማስፋት በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለው ተጠቃሚዎች በገቡት ቃል መሰረት 5 ዓመት ሲሞላቸው መንግስትን አመስግነው ለተተኪዎች ማስረከብ ይኖርባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል። የኢንዱስትሪ ባለቤቶች በበኩላቸው የማምረቻ ቦታዎች ችግር እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል።

የስራ እድል ፈጠራና  የስራ አጥነት ችግር

2

አገራችን ኢትዮጵያ የበለጸገችና መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ በማሰለፍ የህዝቧን የኑሮ ሁኔታ ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሻሻል የሚያስችል መዋቅራዊ አደረጃጀት በመፍጠር ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ሀገራዊ የድህነት ቅነሳ ግብን ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡

የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስቱሪ ልማት ጽ/ቤት የተሰጠውን ስልጣንና እና ኃላፊነት እንዲያሳካ ፖሊሲዎችን፣ ህጐችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በስፋት በማስተዋወቅና በማስፈፀም፣ ኅብረተሰቡን በማሳተፍ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ድጋፍ በማቀናጀት በክ/ከተማችን የሚታየውን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ የሥራ ሥምሪት አገልግሎት በማስፋፋት የሥራ ዕድል እንዲፈጠር በማድረግ ህጋዊ፣ ፍትሃዊና ተደራሽ የዜጎች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በሚያስችል ሁኔታ ወደ ተግባር በመግባት ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የበርካታ ዜጎችን የስራ አጥነት ችግር በመቅረፍ ኑሯቸው እንዲሻሻል እየተደረገ ይገኛል፡፡

l 4

እንዴት የስራ ፈላጊዎችን

ቁጥር መቀነስ ይቻላል?

በክ/ከተማችን የሚታየውን ድህነትና ስራ አጥነት ለመቀነስ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች በምግብ ዋስትና ተጠቃሚ በማድረግ ኑሮአቸውን በማሻሻል፣ በኢንተርፕራይዝ በማደራጀትና በማልማት፣ኢንዱስትሪ ልማት በማስፋፋትና በማበልጸግ የኢንዲስትሪ መር ኢኮኖሚ ሽግግር በማረጋገጥ፣ መንግስታዊ ድጋፎችን በመስጠት፣ በውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ፣ አምራች ዜጎችን ጤንነታቸውንና ደህንነት በማስጠበቅ፣የስራ ቦታና የስራ አከባቢዎችን ምቹ የስራ ሁኔታ በማረጋገጥ ፣ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ በማድረግ ለበርካታ የክ/ከተማችን ነዋሪዎች የስራ እድል መፍጠርና ኑሮ ማሻሻል ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

"ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እየሰራን ነው"
አቶ ጌታሁን ሀ/ማርያም

Lidetapress መጋቢት 15, 2015

በልደታ ክ/ከተማ "ኢትዮጲያ ታምርት" በሚል መሪ ቃል ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ምክክር ተደርጓል። በፕሮግራሙ ሪፖርት ያቀረቡት የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ጌታሁን ሀይለማርያም እንደተናገሩት አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍና በማበረታታት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካትና ወደ ውጭም ኤክስፖርት የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ጌታሁን አክለውም በ1ኛው ኢትዮጲያ ታምርት ንቅናቄ ኢንዱስትሪዎች ሲያነሷቸው የነበሩ ችግሮችን በመቅረፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ተችሏል ሲሉ ገልፀዋል።

በልደታ ክ/ከተማ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ያመረቷቸውን ምርቶች ለእይታ በማቅረብ ማህበረሰቡ በሀገር ምርት እንዲኮራ የሚያስችል ግንዛቤ ፈጥረዋል።

ምቹ የስራ አካባቢዎችን በመፍጠር ሴቶች ውጤታማ እንዲሆኑ መስራት ይገባል ተባለ።

Lidetapress መጋቢት 14, 2015

ምቹ የስራ አካባቢዎችን በመፍጠር ሴቶች ውጤታማ እንዲሆኑ መስራት ይገባል ሲል የልደታ ክፍለ ከተማ የስራ፣ኢንተርፕራይዝና ኢንደስትሪ ልማት ጽ/ቤት ገለፀ። ጽ/ቤቱ አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ "ምቹ የስራ ሁኔታ ለሴት ሰራተኞች" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ አካሂዷል።

4

ምቹ የስራ ሁኔታ ለሴት ሰራተኞች!!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ፣ ኢንተርፕራይዝ ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ የስልጠና ባለሙያ ወ/ሮ አበባ ገብሩ እንደገለጹት ሴቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እንቅስቃሴዎችን በተደራጀ መንገድ በማከናወን የሴቶች ቀንን ከማክበር ባለፈ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዓላማ መሆኑን ጠቁመው የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማሳደግ በሀገራችን ዕድገት የበኩላቸውን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የስራ፣ኢንተርፕራይዝ ኢንደስትሪ ልማት ጽ/ቤት የስራ ስምሪትና ሴፍትኔት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ገብሬ አያሌው እንደተናገሩት ስራዎች ውጤታማ የሚሆኑት የሴቶች ተሳትፎ ማረጋገጥ ስንችል መሆኑን በመጥቀስ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሲከበርም የሴቶችን በስራ ላይ ያላቸውን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ምቹ የስራ አካባቢዎችን በመፍጠር ሊሆን ይገባል ብለዋል።

 a  1

"ድሎችን የማፅናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊ ታሪካዊ አመራሮች ተልዕኮ " ስልጠና...

Lidetapress መጋቢት 12, 2015

በልደታ ክ/ከተማ "ድሎችን የማፅናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊ ታሪካዊ አመራሮች ተልዕኮ " በሚል መርህ ለ2 ቀናት የሚቆይ ስልጠና ለክ/ከተማና ለወረዳ አመራሮች እየተሰጠ ነው።

በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ እንደተናገሩት አመራሩ የአመለካከትና የተግባር አንድነትን ፈጥሮ የተገኙ ስኬቶችን የማፅናትና ፈተናዎችን ደግሞ በጥበብ በማለፍ ወደ ስኬት የመቀየር ኃላፊነቱን መወጣት ይኖርበታል ብለዋል።

የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰይድ ዓሊ በበኩላቸው ብልፅግና ፓርቲ በፈተናዎች ውስጥ እያለፈም ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበ ያለ ፓርቲ ነው ብለው አመራሩ የተገኙ ስኬቶችን ለማፅናት አዳዲስ ስኬቶችን ደግሞ እውን ለማድረግ ከምንጊዜውም በላይ መትጋት ይኖርበታል ሲሉ ገልፀዋል።

የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉእመቤት ታደሰ በበኩላቸው ፓርቲያችን ሰው ተኮር ፓርቲ ነው በመሆኑም ለማህበረሰቡ ሰላም፣ አንድነትና ብልፅግና የሚተጋ ነው ብለው አመራሩ በፓርቲው እሳቤዎች ላይ የጠራ ተልዕኮን በመያዝ ስኬቶችን ለማፅናትና ችግሮችን ለመሻገር መስራት ይገባዋል ሲሉ ገልፀዋል።

ኢንተርፕራይዞቻችንና  የገበያ ትስስር

2 l 4

የጥቃቅን ፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ለኢኮኖሚያዊ ፣ለማህበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት በተለይ ለኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ትግበራ መሳካት ያለውን ፋይዳ ግምት ውስጥ በማስገባት የዘርፉን ዕድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትኩረት በመስጠት እየሰራ ይገኛል።
በዘርፍ ተደራጅተው ለሚሰሩ አንቀሳቃሾች ምርትና ምርታማነታቸውን ማሳደግ የሚያስችሉ መንግስታዊ ድጋፎችን በመስጠት በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ገበያውንም የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ባለፈው በጀት ዓመት በክ/ከተማችን ተደራጅተው የገበያ ትስስር የሚፈልጉ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የገበያ ትስስር ሊፈጠርባቸው የሚችሉ መስኮችን በመለየት የገበያ ትስስር ስራ ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ኢንተርፕራይዞች በገበያ ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲወጡና ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ በገበያ ትስስር ተጠቃሚ በማድረግ በኩል ባሳለፍነው ወራት ውስጥ የተለያዩ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡

የኢንተርፕራይዞች ዉጤታማነት

ለሀገር እድገት መሰረት ነዉ፡፡

በዚህም መሠረት በ2015 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ በሀገር ውስጥ ገበያ ለ708 ኢንተርፕራይዞች የብር 233,725,090.63 የገበያ ትስስር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ታቅዶ ለ999 (>100%) ኢንተርፕራይዞች የብር 229,152,728.48 (98%) የገበያ ትስስር ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ በዉጪ የገበያ ትስስር ለ3 ኢንተርፕራይዞች የብር 1,459,440 የገበያ ትስስር ለመፍጠር ታቅዶ ለ3 (100%) ኢንተርፕራይዞች የብር 4,934,000 (>100%) የገበያ ትስስር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በሀገር ውስጥ ገበያ ትስስር ባሳለፍነው ዘጠኝ ወራት የተሻለ አፈፃፀም ቢኖርም በኢንተርፕራይዝ ለታቀፉ አንቀሳቃሾች በሸማች ማህበራት እንዲተሳሰሩ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በቀጣይ በቂ ትኩረት ልሰጠዉ ይገባል፡፡

አዘጋጅ፡- ማርቆስ ሙላት