የስራ እድል ጥናት እና ፕሮጀክት ዝግጅት

Markos Mulat G Market June 28, 2021

  • መግቢያ

    በከተማችን ያለዉን ዉስብስብ የሆነ ኢከኖሚያዊ ማኅበራዊ እና ሌሎችንም የተለያዩ ችግሮችን ለመፍታትና የህዝቦችን ተጠቃሚነት የስራ ባለቤትንት ለማጠናክር ሁለንተናዊ እድገት አምጭ የሆኑ የልማት እንቅስቃሴዎችን በተጠናከረና በተደራጀ መልኩ ለመፈጸም ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ የጥቃቅንና አነስተኛ አነተርፕራይዞች እስትራቴጂና ፖሊሲ እንዲሁም የተለያዩ የማስፈጸሚያ ደንቦች መመሪያዎች አሰራሮች ተዘርግተዉ ወደ ትግበራ ተገብቷል፡፡ በተለይም ደግሞ የዜጎችን የሥራ እድል በማስፋት እና ከሥራ አጥነት በማላቀቅ ሥራ ፈጣሪነታቸዉንና ምርታማነታቸዉን በማሳደግ ሃገሪቱ በፍጥነት ወደ ኢንዱስትሪ መር የኢኮኖሚ ስርዓት ለመሸጋገር በምታደርገዉ ጥረት ኢንተረፕራይዞች የበኩላቸዉን እንዲወጡ ለማስቻል በጽ/ቤታችን ብሎም በኬዝ ቲማችን ትኩረት ተሰጥቶ የተለያዩ ተግባራትን በመፈጸም ጥረት እየተደረገ ነዉ፡፡

    በ2014 በጀት ዓመትም በወረዳችን ከሚገኘው የስራ አጥ አኳያ የተወሰነውን ለማስተንፈስ በመንግስት ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች፣ በግል ሴክተሮችና በነባር ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ሊፈጠሩ የሚችሉ አማራጭ የስራ ዕድሎችን በማጥናት 2550 በላይ ስራ ዕድል መፍጠር የሚያስችሉ ዕድሎችን በመለየት ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡ በተጨማሪም በባለፈዉ በጀት ዓመት ያልተከናወኑ ተግባራትን ጨምሮ የሴቶችንና ወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና በኢኮኖሚ ግንባታ ዘርፍ የሚጠበቅባቸዉን ሚና እንዲጫወቱ ለማስቻል እንዲሁም ደግሞ ሀብት ፈጣሪ ሆነዉ በቴክኖሎጂ ግንባታ ማስፋፋት፣ በስራ እድል ፈጠራ እና አሁን ላሉንና ወደፊት በሂደት ለሚፈጠሩ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ማቅረብ የሚችሉበትን ሁኔታ ከመፍጠር አንጻር የስራ ዕድል ጥናትና ፕሮጀክት ዝግጅት ኬዝ ቲም በተደራጀ መልኩ ወደ ስራ በማስገባት ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ሲሆን በዚህም አገሪቱና ዜጎቿ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም ሰፊ የሆነ የስራ እድል ለመፍጠርና ዜጎች የስራ ባለቤት በመሆን የበኩላቸዉን በሀገር ኢኮኖሚያዊ ግንባታ የበኩላቸዉን እንዲወጡ ለማስቻል የስራ ዕድል ጥናትና ፕሮጀክት ዝግጅት ኬዝ ቲም ተዘጋጅቷል፡፡

    የዕቅድ ዝግጅት እና ተግባራት አፈጻጸም

    የ2013 በጀት ዓመት ሥራ ሲገመገም አንዱ ችግር ሆኖ የተለየው በለየነው የዳሰሳ ጥናት ልክ ማስተሳሰር አለመቻል እንዲሁም የሚጠኑት ተቋማት በትክክል የተዳሰሱ ናቸው ወይ፤የሚለውን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ከመሆኑ በስተቀር በበጀት ዓመቱ የተቀመጠውን ግብ ከመፈፀም አንፃር የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለሆነም በ2014 የበጀት ዓመት እነዚህንና መሰል ችግሮችን በመፍታትና ያለንን አቅም በሙሉ አሟጠን በአግባቡ ሥራ ላይ ማዋል ፡፡ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ለመፍጠርና አደረጃጀትን ለማጠናከር የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን የማስፋፋትም ሆነ የስራ ዕድል ፈጠራው የአንድ አካል ብቻ ሣይሆን የአስፈጻሚና የባለድርሻ አካላትን የተቀናጀ ተሣትፎ የሚጠይቅ ነው፡፡ በዚህም በወረዳችን ውስጥ የሚገኙ ተቋማት ሆነ ሌሎች የአስፈጻሚና ባለድርሻ አካላት አንድ ዓይነት ግንዛቤ ፈጥረው ማለፍ ይገባቸዋል የሚል ዕምነት አለ፡፡ ምክንያቱም አብዛኛው የኬዝ-ቲማችን ስራ አብዛኛውን አካላት የሚዳስስ ሲሆን በተለይም ከህብረተሰብ ተሳትፎ ኬዝቲም ጋር ተባብሮና ተቀናጅቶ ከመስራቱ አንፃር ክፍተት ነበር ፡፡የቅንጅቱ ዋነኛው ችግር ዕቅድ ዐቅዶ ከመመራትና በመደበኛ የግንኙነት ግዜ እየተገናኙ ስራዎችን ከመስራት አንፃር መሆኑ ይታመናል፡፡

    በዚህም ምክንያት ሥራዎች እንዲንጠባጠቡና በጥራት እንዳይሰሩ ያደረገ ከመሆኑም በላይ ለሰራዊት ግንባታ ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ ሂደት ትልቁ ማነቆ ሆኖ ለማለፍ ችሏል፤በተጨማሪም በወረዳ ደረጃ ሊወያዩ የሚገባቸው ብለን ያሰባሰብናቸው በወረዳ ውስጥ የሚገኙ ታላላቅ ተቋማት በዚህ በጀት ዓመት ውስጥ ከዋና ስራ አስፈፃሚ ጋር በመሆን የሚወያዩበትን መንገድ እናመቻቻለን፡፡ በአጠቃላይ በቀጣይ ዝርዝር አሰራር ተዘጋጅቶለት ሊተገበር የሚገባው ነው፡፡

    የ2014 በጀት ዓመት ቁልፍ እና አበይት ተግባራት ዋና ዋና ግቦችና ተግባራት

    ቁልፍ ተግባር
    የልማት አቅሞችን አደራጅቶ የማስፈፀም አቅማቸዉን በመገንባት በዘርፉ ልማት የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችን በስራ የማደግና የመለወጥ ባህል በማዳበር ልማታዊና ተወዳዳሪ ኢንተርፕራይዞችን በማስፋፋት እና ለአዳዲስ ስራ ፈላጊዎች በተለይ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር በድጋፍ አሰጣጥ የሚታዩ የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባራት በመታገል የፓለቲካል ኢኮኖሚ ለመድፈቅ የሚተጋ የልማት ሰራዊት በመገንባት የዘርፉን ተልዕኮ በላቀ ደረጃ ማሳካት የበጀት ዓመቱ ቁልፍ ተግባራችን ነው፡፡

    የአበይት ተግባራት ግቦችና ዋና ዋና ተግባራት

    ግብ አንድ፡- በመንግስት ግዙፍ ፕሮጀክቶች 28፣ በነባር ጥቃቅንና አነስተኛ 25፣ በመካከለኛና ከፍተኛ ተቋማት 27 በድምሩ በ 80 ተቋማት ዉስጥ የስራ ዕድሎችን በዳሰሳ ጥናት መለየት፤

    ተግባር 1፡ በመንግስት ግዙፍ ፕሮጀክቶች ለ1298 ፣በነባር ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለ677፣ በመካከለኛና ከፍተኛ ተቋማት ለ775 አማራጭ የስራ ዕድሎችን በዳሰሳ ጥናት በመለየት ለ2550 ስራፈላጊዎች የስራ እድል መፍጠር የሚያስችል መረጃ ማሰባሰብ ማጠናቀርና እንዲሰራጭ ይደረጋል፡፡

    ተግባር 2፤ አማራጭ የስራ ዕድል ዳሰሳ ለማካሄድ የሚያስችል ማስፈጸሚያ ዕቅድ በማዘጋጀት መረጃ ማደራጀት፤

    ተግባር 3፤ በማስፈጸሚያ ዕቅዱ ላይ ለወረዳ መዋቅር ግንዛቤ መፍጠር እና የጋራ መግባባት መፍጠር፤

    ተግባር 4፤ ለተለዩ መንግስታዊና የግል ተቋማት በስራ ዕድል ፈጠራ ተሳታፊ እንዲሆኑ በየደረጃው ባለው የጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ መዋቅር አማካኝነት በተለያዩ አግባቦች ማለትም በአካል በመሄድ፣ በደብዳቤ፣ መድረኮችን በማዘጋጀት ጥያቄ ማቅረብ፤ አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ፤ በዚህ ረገድ ባለፉት ዓመታት በስራ ዕድል ፈጠራው የተሻለ አፈጻጸም የነበራቸውን በተለየ አግባብ ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ፤

    ተግባር 5፤ በስራ ዕድል ፈጠራው አጋዥ ለመሆን ፈቃደኝነታቸውን የገለጹ ተቋማትን በክትትል መለየትና የሚፈጠረውን የስራ ዕድል ዓይነት፤ ከስራ ፈላጊው የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎች፣ እና ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን ማደራጀት፤ ሪፖርት ማጠናቀር፤

    ተግባር 6፤ በየደረጃው ባለው መዋቅር የተለዩ የስራ ዕድሎች ውጤታማና ፍሬያማ መሆናቸውን ናሙና በመውሰድ በበጀት ዓመቱ 2 ጊዜ ጥናት ማካሄድ፣ አፈጻጸሙን ማረጋገጥና ለቀጣይ ስራችን ጠንካራና ደካማ ጎኖችን መለየት፤

    ተግባር 7፤ የአስፈጻሚ አካላትን አቅም ለመገንባት እና ለስራ ፈላጊ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር የሚውል 3 ጥናቶች ማድረግ

    ተግባር 8፤ ለዘርፉ ዕድገትና ውጤት ቀጣይነት አዳዲስ የስራ መስክ አማራጮች ላይ 2 ዳሰሳ ጥናትች ይደረጋል፣

    ግብ ሁለት፡- በመደበኛ እና በመንግስት ግዙፍ ፕሮጀክቶች የተለየ ትኩረት በመስጠት ርብርብ በማድረግ በድምሩ ለ2250 ሥራ ለሌላቸዉ ዜጎች በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተ/ዞች ልማት ዘርፍ 80 በመቶ(1800) ቋሚና 20 በመቶ(450) ጊዚያዊ የስራ እድል ይፈጠራል፡፡ ከዚህም ውስጥ 50 በመቶ ሴቶች እና 70 በመቶ ወጣቶች ተጠቃሚ ይደረጋል፡፡

    ተግባር 1፤ የሚፈጠረው የስራ ዕድል ከተቋማት አኳያ፤
    ሀ. በመንግስት ግዙፍ ፕሮጀክት ለ1298 ሰዎች፣
    ለ. በግል ድርጅቶች ለ677 ሰዎች፣
    ሐ. በነባር ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለ775 ሰዎች፣
    በድምሩ ለ2550 ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጠራል ፡፡

    ተግባር 2፤ የሚፈጠረው የስራ ዕድል ከዘርፍ አኳያ፤

    2.1. በመንግስት የልማት ድርጅቶች
    በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለ270፣ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለ226 በአገልግሎት ዘርፍ ለ180 በንግድ ዘርፍ ለ134 እና ከተማ ግብርና ለ88 በድምሩ ለ898 ስራ ፈላጊዎች የስራ እድል የሚፈጥሩ አማራጮች ይለያሉ፡፡

    2.2. በከፍተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች
    በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለ202፣ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለ170 በአገልግሎት ዘርፍ ለ135 በንግድ ዘርፍ ለ102 እና ከተማ ግብርና ለ68 በድምሩ ለ677 ስራ ፈላጊዎች የስራ እድልየሚፈጥሩ አማራጮች ይለያሉ፡፡

    2.3 በነባር የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት
    በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለ203፣ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለ170 በአገልግሎት ዘርፍ ለ 135 በንግድ ዘርፍ ለ101 እና ከተማ ግብርና ለ66 በድምሩ ለ675 ስራ ፈላጊዎች የስራ እድል የሚፈጥሩ አማራጮች ይለያሉ፡፡

    ተግባር 3. በዘርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ ስራ ፈላጊዎች እንዲያግዙ በወረዳ ደረጃ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ 1፣ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ፣ በከተማ ግብርና ዘርፍ ፣ በአገልግሎት ዘርፍ፣ በንግድ ዘርፍ፣ በድምሩ አማራጭ የስራ እድሎችን የሚያሳዩ ፕሮጀክት ፕረፖዛሎች ይዘጋጃሉ፡፡
    1. የጥናት ርዕሶችን መለየት፤
    2. ፕሮፓዛል ማዘጋጀት፣
    3. መረጃ መሰብሰብ የሚያስችሉ መጠይቆችን ማዘጋጀት፤
    4. መረጃዎችን መሰብሰብና መተንተን
    5. የጥናት ሠነዱን ማጠናቀቅ
    6. የጥናት ሠነዶቹን የሚመለከታቸው አካላቶች በተገኙበት መወያየት እና ለቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተግባራዊ ማድረግ፣

    ተግባር 4. በዘርፉ መደራጀት ለሚፈልጉ ስራ ፈላጊዎች እንዲያግዙ በወረዳ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ 1፣ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ፣ በከተማ ግብርና ዘርፍ ፣ በአገልግሎት ዘርፍ 1፣ በንግድ ዘርፍ ፣ በድምሩ 2ሞዴል የንግድ እቅዶች ይዘጋጃሉ፡፡

    ግብ ሶስት፡ ልዩ ትኩረትና ድጋፍ ከሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ለሴቶች፣ ለወጣቶች፣ ለአካል ጉዳተኞ ዜጎች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ ተግባራትን ማጎልበት ታቅዷል፡፡

    ተግባር 1. የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ እንዲያስችል ሴቶች በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ንቁ፣ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ተቋማት፣ ከሴት የህዝብ አደረጃጀቶች፣ ከትምህርት ተቋማትና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የተለያዩ የግንዛቤ መስጫ መድረኮችን በማዘጋጀትና በሌሎች አካላት የሚዘጋጁትን በመጠቀም ስለ ጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ስትራቴጂና በዘርፉ የተፈጠሩ ዕድሎችን እንዲሁም ምቹ ሁኔታዎችን ማስገንዘብ፤

    ተግባር 2. የሴቶች አደረጃጀቶችን (ሊግ፤ ማህበር ፎረም እና ፌደሬሽን) በመጠቀም በእያንዳንዱ አደረጃጀት ዓይነት የሚሳተፉ ስራ ፈላጊ አባሎቻቸውና አባል ባልሆኑ ሴቶች የሚታየውን የስራ ማማረጥ አመለካከት ችግር ለመቀነስ ተከታታይ የሆነ የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲመጣና በዘርፉ ተደራጅተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚስችል ተግባር ማከናወን፣ ማበረታታት፤

    ተግባር 3. በሁሉም የጥቃቅንና አነስተኛ እድገት ተኮር ዘርፎች የሴቶች ተጠቃሚነት በእኩል ደረጃ እንዲሆን በማድረግ፣ ከመንግስት አውትሶርስ ተደርገው ለስራ ዕድል ፈጠራ በሚቀርቡ እንደ ፓርኪንግ አገልግሎት፣ የጽዳትና ውበት ስራዎች፣ የኮብልስቶን ንጣፍ ስራዎች፣ ወዘተ ሴቶች በላቀ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ስርዓት በመቀየስ አጠቃላይ ከሚፈጠረው የስራ እድል የሴቶች ተጠቃሚነት 50 በመቶ እንዲሆን ማድረግ፤

    ተግባር 4. ለ5 አካል ጉዳተኞች ስለ ስራ ፈጠራ ግንዛቤ በመፍጠር የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡

    ማጠቃለያ

    በክ/ከተማችን ያሉ መንግስታዊ መንግስታዊ ያልሆኑ እና በጥቃቅን ና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ተደራጅተዉ አቅም የፈጠሩና የተሸጋገሩትን በመለየት የስራ እድል ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ በሥራ ፈላጊነት ለሚመዘገቡ 2550 ስራ ፈላጊዎች የስራ እድል በማመቻቸት ወደ ስራ ማስገባት ፡፡ የዘርፉን መረጃዎች በማሰባሰብና በመተንተን ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ ፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነትን በተጠናከረ አኳኋን ለመዋጋት የልማት ስራዎቻችንን በልማት ሰራዊት እንዲመሩ በማድረግ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ትኩረት በመስጠት የወጣቶችና የሴቶችን የስራ ዕድል ተጠቂሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ ስራዎቻችን በተጠናከረ የኮሚንኬሽን ስራ በማስደገፍና የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እንዲደገፉ በማድረግ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ጥረት እናደርጋለን፡፡