በልደታ ክ/ከተማ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስቱሪ ልማት ጽ/ቤት የተከናወኑ ስራዎች ዜና
በልደታ ክ/ከተማ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስቱሪ ልማት ጽ/ቤት የተከናወኑ ስራዎችን በፎቶ
በልደታ ክ/ከተማ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስቱሪ ልማት ጽ/ቤት የተከናወኑ ስራዎች በቪዲዮ
በልደታ ክ/ከተማ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስቱሪ ልማት ጽ/ቤት መግለጫዎች
የኢንተርኘራይዞችንና የኢንደስትሪ ልማት ለማፋጠን የሚረዱ ተቋማዊ ስትራቴጂዎች፣ ስልቶችን፣ ፕሮግራሞችን፣ ፕሮጀክቶችን፣ የድጋፍ ማዕቀፎች፣ መመሪያዎችንና እቅዶችን ያዘጋጃል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
በክ/ከተማው ውስጥ የሚገኙትን ነዋሪዎች አምራች ዜጋ ለማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ የስራ ዕድል አማራጮችን ይለያል፣ ያጠናል፣ ያስጠናል፣ ፕሮጀክት ፕሮፋይል ያዘጋጃል፣ የአዋጭነት ጥናቶችን ያጠናል፣ ያስተዋውቃል፣ ወደ ስራ እንዲገቡ ያበረታታል፤
የኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነት በቀጣይነት ሊያሣድጉ የሚችሉ የአቅም ግንባታ እና ችግር ፈቺ የጥናት ስራዎችን ያከናውናል፤ እንዲሁም የሰራተኞች የስራ ላይ ደህንነት፤ የአካባቢ ጥበቃና የኢንዱስትሪ ሰላም የሚያስጠብቁ ተግባራትን ያከናውናል፣፣
ኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች ለተወዳዳሪነታቸው እንቅፋት የሆኑ ጉዳዩችን በጥናት በመለየት መፍትሔ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ ምርጥ ተሞክሮዎችን ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር ለይቶ ያጠናል፣ ይቀምራል፣ ያስተገብራል፣ ውጤታማነቱን ይከታተላል.
የኢንተርኘራይዞችና ኢንደስትሪዎችን የገበያ ችግር ለመቅረፍ ከተለያዩ አካላት ጋር የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው ያደርጋል፤ ኤግዚቢሽንና ባዛሮች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤ በውጭ ሀገር በሚካሄዱ ኤግዚቢሽንና ባዛሮች እንዲሳተፉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
ኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች የመረጃ፣ የቴክኖሎጂ መረጣ፣ የድርድር፣ የግንባታ፣ የኮሚሺኒንግ ድጋፍ ይሰጣል፤ ውጤቱንም ይገመግማል፤ የመረጃና የምክር አገልግሎት የሚሰጥበት የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፤ የብቃት ማረጋገጫ እንዲሁም የደረጃ እና የጥራት ሰርቲፊኬሽን እንዲያገኙ ድጋፍ ያደርጋል፤
በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች የአምራችነት ፍቃድ ይሰጣል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ በህጉ መሰረት ሳይሰራበት ሲቀር ፍቃዱን ይሰርዛል፣ በሰጣቸው የአምራችንት ፍቃድ መሰረት የማምረት አቅም ይለካል፣ የምርት ጥራት ቁጥጥርና ኢንስፔክሸን ስራዎችን ይሰራል፣
መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ እና ከግል ድርጅቶች ጋር ትስስር በመፍጠር ኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች ድጋፍ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣ተፈጻሚነቱን ያረጋግጣል፤
ከማህበረሰብ አቀፍ ልማት ስራዎች የተጠቃሚነት ጊዜያቸው ሲያበቃ የማስመረቅ ስራ ይሰራል፤ በዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
መስራት እየቻሉ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት ሥራ ሳይኖራቸው በከፋ ድህነት ላይ የሚኖሩ የከተማ ነዋሪዎችን መረጃ ይመዘግባል፤ ይለያል፤ ያደራጃል፤ ይተነትናል፤ ሲፈቀድለትም በማህበረሰብ አቀፍ ልማት ስራዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
ለኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች አገልግሎት እንዲውሉ የተዘጋጁ ነባር የመስሪያ ቦታ የሆኑ ህንጻዎች፣ ሼዶች፣ ተለጣፊ ሱቆች እና ኮንቴነሮች እንዲሁም በመንግስት፣ በግልና በተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች የተገነቡ መደብሮችን ያስተዳድራል፤ ይከታተላል፤
ኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች ማምረቻ፣ ማሳያ እና መሸጫ ሼድና ህንጻ በኢንደስትሪ መንደሮች፣ በክላስተር ማዕከላት፣ በገበያ ማዕከላት እና በኢንፖሪየም ማዕከላት በማደራጀት እንዲገነቡ ያደርጋል፤ እድሳትና ጥገና እንዲደረግላቸው ያደርጋል፤ የመሠረተ ልማት አውታሮችም እንዲሟሉላቸው ይደግፋል፤ ይከታተላል፤
ለኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች ማምረቻ፣ ማሳያ እና መሸጫ ሼድና ህንጻ በኢንደስትሪ መንደሮች፣ በክላስተር ማዕከላትና በገበያ ማዕከላት ማስገንባት እንዲችል ከሚመለከተው አካል የለማ መሬት ይረከባል፤ ካርታ የሌላቸው ነባር ይዞታዎች ካርታ እንዲሰራላቸው ያመቻቻል፤ የተገነቡትን ያስተላልፋል፤ ያስተዳድራል፤
በ2022 በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክ/ከተማ ሰፊ የስራ ዕድልና የተሻለ...
በዘርፉ እድገት የሚጠበቀውን አስተዋጽዖ ለማበርከት በሥሩ...
በዘርፉ እድገት የሚጠበቀውን አስተዋጽዖ ለማበርከት በሥሩ..
በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት የተገልጋዮችን እርካታ..
ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በማስተባበር ለዜጎች...
በክ/ከተማው ውስጥ የሚገኙትን ነዋሪዎች አምራች ዜጋ ለማድረግ...