መግቢያ

የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማስተባባሪያ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የተሰጠውን ሰልጣንና እና ኃላፊነት እንዲያሳካ በከተማ ደረጃ ጥናት በማካሄድ ፖሊሲዎችን፣ ህጐችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በስፋት በማስተዋወቅና በማስፈፀም፣ ኅብረተሰቡን በማሳተፍ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ድጋፍ በማቀናጀት የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ግብዓት እንዲሟላ ማድረግ፣የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች በአንድ ማዕከል ስታንዳርድ መሰረት እንዲፈፀም ድጋፍ ማድረግ የመረጃ አስተዳደር እና መረጃ ስርጭት ማዕከል ማደራጀት፤ዘመናዊ የመረጃ ስርዓት እንዲዘረጋ ማድረግ፣መረጃዎችን ማደራጀት፣መተንተን፣ማሰራጨት፣እና መንግስታዊ ድጋፎችን ድጋፎችን በአንድ ማዕከል አገልግሎት በመስጠት ህጋዊ፣ ፍትሃዊና ተደራሽ የዜጎች ተጠቃሚነትን በሚያስችል መልኩ እና ተገልጋዩ ህብረተሰብ የሚጠብቀውን የመጨረሻ ውጤት የሚመለከቱ ተያያዥነት ያላቸው አገልግሎቶች ተደራሽ በሆነ እና በተቀናጀ አገባባ በአንድ ዳይሬክቶሬት እንዲጠቃለሉና እንዲደራጁ ተደርጓል፡፡

የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ መርሆዎች

  1. ለሰራ ፈላጊ ዜጎች እና ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጡ አገልግሎቶች ተደራሽነትን ማረጋገጥ፤ የሚሰጡ አገልግሎቶች የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችና ስራ ፈላጊዎች ፍላጎት መሠረት ያደረጉ እንዲሆኑ ማስቻል፣
  2. ሁሉም ለስራ ፈላጊዎቸና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጡ አገልግሎቶች በተቀናጀና በተደራጀ አግባብ ወጪና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ መልኩ እንዲሰጡ ማድረግ፤
  3. የአንድ ማዕከሉ አገልግሎት ሰራተኞች የስነ ምግባር መርሆዎችን የተላበሱና ለሚሰጡትም አገልግሎት ኃላፊነት፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖራቸው ማድረግ፤
  4. በአንድ ማዕከሉ የሚሰጡ አገልግሎቶች የሴቶችና ወጣቶችን፣ የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እንዲሆኑ ማስቻል፣
  5. በአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጡ አገልግሎቶች ለማን፣ መቼና እንዴት እንደሚሰጥ ለተጠቃሚዎች ግልፅነት የመፍጠርና ልማታዊ አስተሳሰቦችን ማስፈን፤

በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ለስራ ፈላጊ ዜጎች እና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች

የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የምክር አገልግሎት መስጠት ፣

  1. የቢዝነስ ፕላን ዝግጅት ድጋፍ አገልግሎት መስጠት፤
  2. ሞዴል የንግድ ስራ ዕቅድ ማቅረቢያ ቅፅ አዘጋጅቶ የማቅረብ አገልግሎት መስጠት ፣
  3. በንግድ ምዝገባና ፈቃድ ለማውጣት የሚያስችሉ መስፈርቶች ላይ ግንዛቤ መፍጠር፣
  4. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥርና ምስክር ወረቀት ለማግኘት የሚያስችሉ መስፈርቶች ላይ ግንዛቤ መፍጠር ፣
  5. በግብር አዋጆች ፣ ደንቦች እና መመርያዎች ግንዛቤ መፍጠር ፣
  6. ለሰልጣኞች የብቃት ምዘና ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ለማውጣት የሚያስችል ግንዛቤ መፍጠር ፣
  7. የብድርና ቁጠባ ምክር አገልግሎት መስጠት እና አገልግሎት አማራጮች ላይ ግንዛቤ መፍጠር፣
  8. የመሳሪያ ሊዝ ኪራይ አገልግሎትን በተመለከት ግንዛቤ ማስጨበጥ፣ ጥያቄ ለሚያቀርቡ ኢንተርፕራይዞች አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲያሟሉ የምክር አገልግሎት የመስጠት ፤
  9. በኢንተርፕራይዞች ፍላጎት የተለዩት የካፒታል ዕቃዎች ከተጠቃሚዎቹ ጋር በመሆን መስፈርታቸውን አዘጋጅቶ መስጠት፤
  10. ንግድ ፈቃድ ለማውጣት የሚያስፈልጉ ብቃት ማረጋገጫ መስፈርቶች እና ስለሚሟሉበት ሁኔታ ግንዛቤ መስጠት፣
  11. በከተማ ግብርና ዘርፍ ንግድ ፈቃድ ለማውጣት የሚያስፈልጉ የብቃት ማረጋገጫ መስፈርቶችና ስለሚሟሉበት ሁኔታ ግንዛቤ መስጠት፣
  12. መስሪያ ቦታዎች ተጠቃሚ የሚሆኑትን ኢንተርፕራይዞች አስፈላጊ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ ምክር አገልግሎት መስጠት ፤

የምዝገባና መረጃ አገልግሎት መስጠት ፤

  1. በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የሚሰጡ አገልግሎቶችንና አገልግሎቶችን ለማግኘት ባለጉዳዮች ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶችና የአሰራር ቅደም ተከተሎች መረጃ መስጠት ፣
  2. ስራ ፈላጊ ዜጎችን በባህር መዝገብ በመመዝገብ የስራ ፈላጊ መለያ መታወቂያ ካርድ መስጠት እና የተመዘገቡትን ስራ ፈላጊዎችን በዘመናዊ የመረጃ ቋት ማስገባት ፣
  3. በአንድ ማዕከል ከተደራጁ ሥራ ፈላጊዎች መካከል በየደረጃው የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸውን የወስዱትን የሥራ ፈላጊነት መታወቂያ ካርድ እንዲመልሱ ለማድረግ፤
  4. ወደ ሥራ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ተገልጋዮች የሥራ ዕድል አማራጮችን እና ቅድመ ሁኔታዎችን የማመቻቸት አገልግሎት መስጠት፤
  5. ወደ ሥራ ለመሰማራት ህጋዊ የአደረጃጀት አማራጮች እና የመንግስት የድጋፍ ማዕቀፎች እንዳሉ መረጃ መስጠት፤
  6. በገበያ አዋጪና ተፈላጊ የሆኑትን የስራ መስኮች፣ የስልጠና አይነት፣ የቆይታ ጊዜና ቦታ መረጃ መስጠት፣
  7. የገበያ ትስስር ጥያቄ መቀበል፣ የገበያ ጥናት መረጃ መስጠት፤
  8. በተለያዬ ምክንያት ጥገናና እድሳት የሚያስፈልጋቸው የመስሪያ ቦታዎች ጥገናና ዕድሳት አገልግሎት ለማግኘት የሚቀርብ ጥያቄ መቀበል ፤
  9. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ሰርተፍኬት አወጣጥ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን መስጠት፤
  10. የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አወጣጥ መረጃዎችን መስጠት፤
  11. የንግድ ነክ መረጃ መስጠት፤
  12. ተገልጋዮች በዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጅ በመጠቀም አገልግሎቶችን ማግኘት የሚችሉበትን መረጃ መስጠት ፣

ህጋዊ አደረጃጀት በመፍጠር ለስራ ዝግጁ የማድረግ አገልግሎት መስጠት ፣

  1. ሥራ ፈላጊዎችን መመዝገብ፤ የስራ አጥነት ካርድ መስጠት፤
  2. ስራ ፈላጊዎችን በሚፈልጉት የአደረጃጀት ዓይነት ማደራጀት፣
  3. የመመስረቻ ጽሑፍና መተዳዳሪያ ደንብ ረቂቅ ሰነድ እና ቅፃቅፆች ናሙና መስጠት፤
  4. በህብረት ሽርክና ማህበር እና በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለሚደራጁ እና ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የመመስረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ የድጋፍ አገልግሎት መስጠት ፣
  5. በህብረት ሽርክና ማህበር እና በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለሚደራጁ ኢንተርፕራይዞች የመመስረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ እንዲጸድቅ የማመቻቸት አገልግሎት መስጠት ፣
  6. በህብረት ሽርክና ማህበር እና በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለሚደራጁ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ የውሳኔ ሃሳቦች ማሻሻያዎች ሙያዊ ድጋፍ አገልግሎት መስጠት፣
  7. በህብረት ሽርክና ማህበር እና በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለሚደራጁ እና ለተደራጁ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ቃለ ጉባኤ እንዲጸደቅ የማመቻቸት ድጋፍ አገልግሎት መስጠት ፣
  8. የንግድ ስያሜ ፤ የንግድ የድርጅት ስም ፤ የንግድ ምዝገባ ፤ አዲስ የንግድ ስራ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት፤

የድጋፍ አገልግሎት መስጠት ፣

  1. አዋጪ የቢዝነስ ፕላን ዝግጅት ድጋፍ መስጠት ፣
  2. ለጀማሪ ኢንተርፕራይዞች የእድገት ደረጃ ማሳወቂያ ምስክር ወረቀት መስጠት ፣
  3. የክህሎት ስልጠና ድጋፍ ማመቻቸት፤
  4. የመሥርያ ቦታ ኪራይ ውል የማዋዋል እና የማደስ አገልግሎት መስጠት፤
  5. የብቃት ማረጋገጫና ምዘና ማዕከሉ ለአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የላከውን ተመዝነው ብቁ የሆኑትን ሰልጣኞች የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለባለጉዳዮች መስጠት፣
  6. የደረሰኝ ህትመት ፈቃድ አገልግሎት መስጠት፣
  7. ብድር መስጠት፤ ቁጠባ እንዲቆጥቡ ማድረግ ፣ ብድር ማስመለስ ፣
  8. የዘርፍ ለውጥ፣ ካፒታል ማሻሻያ፣ የስም ለውጥ፣ አድራሻ ለውጥ እና የስራ አስኪያጅ ለውጥ ማድረግ፣

  9. ለበለጠ መረጃ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ይጫኑ።


ተያያዥ መረጃዎች
© 2023 Lideta Subcity Job Creation. Designed by Markos Mulat G