መግቢያ

አገራችን ኢትዮጵያ የበለጸገችና መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ በማሰለፍ የህዝቧን የኑሮ ሁኔታ ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሻሻል የሚያስችል መዋቅራዊ አደረጃጀት በመፍጠር ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ሀገራዊ የድህነት ቅነሳ ግብን ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡

መንግስት ሀገራችን ከነበረችበት ድህነትና ኋላቀርነት ለማላቀቅ የህብረተሰቡን የኢኮኖሚና ማህበራዊ የላቀ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ዘርፎችን እየለየና በሂደት ዘርፉን ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በመቅረጽና ወደ ተግባር በመግባት ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የበርካታ ዜጎችን የስራ አጥነት ችግር በመቅረፍ ኑሯቸው እንዲሻሻል እየተደረገ ይገኛል፡፡ ለከተማ ነዋሪው ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ከመስጠት እና ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር አንጻር መንግስት ባደረገው ጥናት መሰረት ክፍተት የነበረበት በመሆኑ በተለያዩ ተቋማት ሲሰጡ የነበሩ ተግባርና ኃላፊነት ወደ አንድ በማምጣት ለተገልጋዮች የተሻለ አግልግሎት ለመስጠት እንዲያስችልና የከተማ አስተዳዳሩ ራዕይ በተሻለ ሁኔታ ለማሳካት ታሳቢ በማድረግ ተቋማቱ ወደ አንድ እንዲመጡ ተደርጓል፡፡

በከተማ የሚታየውን ድህነትና ስራ አጥነት ለመቀነስ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች በምግብ ዋስትና ተጠቃሚ በማድረግ ኑሮአቸውን በማሻሻል፣ በኢንተርፕራይዝ በማደራጀትና በማልማት፣ኢንዱስትሪ ልማት በማስፋፋትና በማበልጸግ የኢንዲስትሪ መር ኢኮኖሚ ሽግግር በማረጋገጥ፣ መንግስታዊ ድጋፎችን በመስጠት፣ በውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ፣ አምራች ዜጎችን ጤንነታቸውንና ደህንነት በማስጠበቅ፣የስራ ቦታና የስራ አከባቢዎችን ምቹ የስራ ሁኔታ በማረጋገጥ ፣ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ በማድረግ ለበርካታ የከተማችን ነዋሪዎች የስራ እድል መፍጠርና ኑሮ ማሻሻል ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

አግሮ-ፕሮሰሲንግና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክቶሬት የወጣን ሕግ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ ስትራቴጂና የድጋፍ ማዕቀፍ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን እንዲሁም የምርት ጥራትን ለማረጋገጥ ተወዳዳሪነትን መሰረት ያደረገ አሰራርን በመከተል ገቢ ምርትን ለመተካት እና ኤክስፖርት ለማድረግ የሚያስችል የቴክኒክና ክህሎት፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና መረጣ፣ ድርድርና ኮሚሽንግ፣ በኢንዱስትሪ ኤክስተንሸን ምክርና ድጋፍ አገልግሎት በመስጠት፤ የምርት ስታንዳርድ፣ የብቃት ማረጋገጫ፣ የደረጃና ጥራት ሰርተፍኬት እንዲኖራቸዉ እንዲሁም በኢንዱስትሪዎች መካከል የእዉቀት፣ የክህሎትና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር ሥራዎችን ያከናውናል፡፡

የስራ ሂደቱ መነሻ፡-

የስራ ሂደቱ መነሻ፡- የኢንዱስትሪዎች የቴክኒካል ክህሎት፣ የቴክኖሎጂ፣ የፋይናንስ፣ የካፒታል ሊዚ፣ ምርት ጥራትና ምርታማነት የድጋፍ ጥያቄ

የስራ ሂደቱ መነሻና መድረሻ፡-

የስራ ሂደቱ መነሻና መድረሻ፡- በምርትና ምርታማነት፣ በጥራትና በዋጋ ተወዳዳሪ የሆነ አምራች ኢንዱስትሪ

ተያያዥ መረጃዎች
© 2023 Lideta Subcity Job Creation. Designed by Markos Mulat G