የልደታ ክ/ከተማ የኑሮ ውድነትና የገበያ ማረጋጋት ግብረ-ሀይል በእሁድ ገበያው ያለውን የምርት አቅርቦትና የግብይት ሁኔታ ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።

የክ/ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የግብር ሀይሉ ሰብሳቢ አቶ ብርሀኑ ኤኬታ ገበያውን ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት እንደተናገሩት በእሁድ ገበያው የግብርና ምርቶች በበቂ ሁኔታ መቅረባቸውንና ማህበረሰቡም ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እየሸመተ መሆኑን ማየት ችለናል ብለዋል።

አቶ ብርሀኑ አክለውም ከግብርና ምርቶች በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ምርቶችም በበቂ ሁኔታ መቅረባቸውን ገልፀው ግብረ ሀይሉ ተግባሩን በቅርበት እየተከታተለ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

ምልከታ ባደረግንባቸው ገበያዎች ህብረተሰቡ ያለምንም መጨናነቅ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እየሸመተ ነው ያሉት አቶ ብርሀኑ የምርቶች የዋጋ ዝርዝር ተለጥፎ በተለጠፈው መሰረት ግብይት እየተካሄደ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

ምንጭ ፡- የልደታ ክ/ከተማ ኮሙኑኬሽን ጽ/ቤት።
ተያያዥ መረጃዎች
© 2023 Lideta Subcity Job Creation. Designed by Markos Mulat G