አምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርቶችን በማምረትና በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ሆነው በመቅረብ በኢኮኖሚ እድገት ላይ አስተዋፆ ሊያደርጉ ይገባል ሲል የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገለፀ። በአስተዳደሩ " ኢትዮጲያ ታምርት " በሚል መሪ ቃል ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ ንግግር ያደረጉት የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰይድ ዓሊ እንደተናገሩት አምራች ኢንዱስትሪዎች ያለንን ፀጋ ተጠቅማቹህ ጥራት ያላቸው ተኪ ምርቶች በማምረት በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ልትሆኑ ይገባል ብለው ድህነትንና ኃላ ቀርነትን ለማሸነፍ የእናንተ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋልና በህብረት በርትታቹህ መክራት ይኖርባቹሃል ሲሉ ተናግረዋል። አምራች ኢንዱስትሪዎች ሰርታቹህ፣ ያላቹህን እውቀት አጎልብታቹህና ቴክኖሎጆን ተጠቅማቹህ ለውጥ በማምጣትና አቅም በመፍጠር ሽግግር ማድረግ ይገባቹሃል ያሉት ስራ አስፈፃሚው በመተባበርና በመደጋገፍ ሰርተን የኢኮኖሚ ጥገኝነታችንን ከቀየርን ኢትዮጲያ ታድጋለች ትበለፅጋለች ብለዋል።

የክ/ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሀኑ ኤኬታ በበኩላቸው የመስሪያ ቦታዎችን ህጋዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ይገባል ፤ 5 ዓመት የሞላው ተጠቃሚ ለተተኪ የስራ እድል ተጠቃሚዎች መልቀቅ ይኖርበታል ብለው ለማደግና ለመለወጥ እኔ ብቻ ከሚል አስተሳሰብ ወጥተን መስሪያ ቦታዎችን ለተተኪዎች በመልቀቅና ተጋግዘን በመስራት መለወጥ አለብን ሲሉ ተናግረዋል። በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢዘዲን ሙስብሀ በበኩላቸው መንግስት የመስሪያ ቦታዎችን ለማስፋት በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለው ተጠቃሚዎች በገቡት ቃል መሰረት 5 ዓመት ሲሞላቸው መንግስትን አመስግነው ለተተኪዎች ማስረከብ ይኖርባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል። የኢንዱስትሪ ባለቤቶች በበኩላቸው የማምረቻ ቦታዎች ችግር እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል።

በእለቱም ተኪ ምርትና ኤክስፖርት ምርት ላመረቱና የስራ እድል ለፈጠሩ ኢንተርፕራይዞች እውቅና ተሰጥቷል።

ተያያዥ መረጃዎች
© 2023 Lideta Subcity Job Creation. Designed by Markos Mulat G