በልደታ ክ/ከተማ "ድሎችን የማፅናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊ ታሪካዊ አመራሮች ተልዕኮ " በሚል መርህ ለ2 ቀናት የሚቆይ ስልጠና ለክ/ከተማና ለወረዳ አመራሮች እየተሰጠ ነው። በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ እንደተናገሩት አመራሩ የአመለካከትና የተግባር አንድነትን ፈጥሮ የተገኙ ስኬቶችን የማፅናትና ፈተናዎችን ደግሞ በጥበብ በማለፍ ወደ ስኬት የመቀየር ኃላፊነቱን መወጣት ይኖርበታል ብለዋል።

የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰይድ ዓሊ በበኩላቸው ብልፅግና ፓርቲ በፈተናዎች ውስጥ እያለፈም ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበ ያለ ፓርቲ ነው ብለው አመራሩ የተገኙ ስኬቶችን ለማፅናት አዳዲስ ስኬቶችን ደግሞ እውን ለማድረግ ከምንጊዜውም በላይ መትጋት ይኖርበታል ሲሉ ገልፀዋል።

የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉእመቤት ታደሰ በበኩላቸው ፓርቲያችን ሰው ተኮር ፓርቲ ነው በመሆኑም ለማህበረሰቡ ሰላም፣ አንድነትና ብልፅግና የሚተጋ ነው ብለው አመራሩ በፓርቲው እሳቤዎች ላይ የጠራ ተልዕኮን በመያዝ ስኬቶችን ለማፅናትና ችግሮችን ለመሻገር መስራት ይገባዋል ሲሉ ገልፀዋል።

ተያያዥ መረጃዎች
© 2023 Lideta Subcity Job Creation. Designed by Markos Mulat G