በ2015 በጀት ዓመት በ8 ወራት ዉስጥ በክ/ከተማችን ተደራጅተው የገበያ ትስስር የሚፈልጉ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የገበያ ትስስር ሊፈጠርባቸው የሚችሉ መስኮችን በመለየት የገበያ ትስስር ለመፍጠር የተለያዩ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡

በዚህም መሠረት በ8 ወራት በሀገር ውስጥ ገበያ ለ1182 ኢንተርፕራይዞች የብር 324,041,106 የገበያ ትስስር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ታቅዶ ለ1034 (87%) ኢንተርፕራይዞች የብር 324,041,106 (89%) የገበያ ትስስር ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ በዉጪ የገበያ ትስስር ለ4 ኢንተርፕራይዞች የብር 6,217,600 የገበያ ትስስር ለመፍጠር ታቅዶ ለ4 (100%) ኢንተርፕራይዞች የብር 6,614,000 (>100%) የገበያ ትስስር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

በሀገር ውስጥ ገበያ ትስስር በ8 ወራት የተሻለ አፈፃፀም ቢኖርም በኢንተርፕራይዝ ለታቀፉ አንቀሳቃሾች በሸማች ማህበራት እንዲተሳሰሩ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በቀጣይ በቂ ትኩረት ልሰጠዉ ይገባል፡፡

በተጨማሪም በዘርፍ ተደራጅተው ለሚሰሩ አንቀሳቃሾች ምርትና ምርታማነታቸውን ማሳደግ የሚያስችሉ መንግስታዊ ድጋፎችን በመስጠት በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ገበያውንም የማረጋጋት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡

ተያያዥ መረጃዎች
© 2023 Lideta Subcity Job Creation. Designed by Markos Mulat G