የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ያዘጋጀው አገር አቀፍ የሞዴል ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽን እና ባዛር በስኬት ተጠናቋል። በመዝጊያ ሥነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው የኢንተርፕራይዞቹን ቆይታ በጋራ የገመገሙት በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ፣ስራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን የባዛሩ ቆይታ ስኬታማ እንደነበር በመጥቀስ ከኢንተርፕራይዞቹ በተሰጠን አስተያየት መሠረት የሚቀጥለውን ከዚህ በተሻለ ሁኔታ እናዘጋጃለን ብለዋል።

የጊዜውን ማጠር እና በዓመት አንድ ጊዜ ባይሆን በሚል ኢንተርፕራይዞቹ ላነሱት ጥያቄ በአዲስ አበባ ጀሞ አንድ ላይ የከተማ አስተዳደሩ በቋሚነት ባዛር እንዲካሄድበት የሰጠውን ቦታ ለመገንባት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

ባዛሩ ተሳታፊዎቹ ከመንግስት ድጋፍ ተደርጎላቸው ምርቶቻቸውን ሸጠው እንዲሸጋገሩ ማድረግን እንደልዩ ዓላማ የያዘ በመሆኑም ከዕቅዱ አንፃር ስኬታማ ነበር ብለዋል። በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ነቢሃ መሀመድ በበኩላቸው ኢንተርፕራይዞቹ የነገ ተስፋዎች መሆናቸውን አስታውሰው በዓለማቀፍ ገበያ በመግባት ምርቶቻቸውን በማስተዋወቅ በውጭ ምንዛሪም አገራቸውን እንዲደግፉ አሳስበዋል።

ባዛሩ በተሳትፎም ሆነ ከዓላማው አኳያ ጥንካሬና ድክመቶቹን በመለየት ለቀጣዩ ባዛር ለመዘጋጀት ምቹ ሁኔታ የፈጠረ መሆኑን ገልፀዋል። በባዛሩ ለተሳተፉ 186 ኢንተርፕራይዞች እና 8 ተቋማት ምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን 94በመቶ የታለመለትን ግብ እንዳሳካ ተገልጿል።

ምንጭ ፡- የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ
ተያያዥ መረጃዎች
© 2022 Lideta Subcity Job Creation. Designed by Markos Mulat G