በልደታ ክፍለ ከተማ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስቱሪ ልማት ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት በ8 ወራት ዉስጥ በመደበኛ ፤ በመንግስት ግዙፍ ፕሮጀክቶች እና በግል ተቋማትና በመንግስት መዋቅር ቅጥር የተለየ ትኩረት በመስጠት ርብርብ በማድረግ በድምሩ ለ27239 ሥራ ለሌላቸዉ ዜጎች በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፍ 80 በመቶ(24226) ቋሚና 20 በመቶ(2953) ጊዚያዊ የስራ እድል በድምር 27,184 ተፈጥሯል፡፡

የስራ እድል ተጠቃሚ የሚሆኑ ወጣቶችን ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ስልጠና እንዲወስዱ ተደጓል፡፡ በዚህም በበጀት ዓመቱ 3152 ስራ ፈላጊዎችን ለማሰልጠን ታቅዶ 5298 ስራ ፈላጊዎች በተለያዩ የሙያ መስኮች የሙያ ክህሎት ስልጠና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ጋር በመቀናጀት እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡

የሥራ ባህልን ለማጎልበት በዘርፉ የህዝብ ተሳትፎ / ሞቢሊይዜሽን/ እና ሥልጠና ስራ በተደራጀና በመዋቅር እንዲፈጸም በማድረግ 24516 ስራ ፈላጊዎችን መመዝገብና ወደ ስራ የማስገባት ስራ ተሰርቷል።

በሰው የመነገድ እና በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላለከል ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል፡፡

በ8 ወራት ዉስጥ አማራጭ የስራ እደል የሚፈጥሩ መስኮችን የመለየት አፈፃፀሙ የተሻለ ቢሆንም የተለዩትን አማራጮች ሂደት ከመቁጠር ውጭ ወደ ተግባር አለመቀየር፣ በግል ተቋማት ስራ ለመቅጠር የሚያቀርቡት የደመወዝ መጠን አነስተኛ የመሆን፣ ድርጅቶቹ የሚጠይቁትን የሰለጠነ የሰው ሃይል በወቅቱ ማቅረብ አለመቻል፣ የስራ እድል እንፈጥራለን ያሉ ተቋማት ባቀዱት መሰረት ስራ አለመፍጠርና የስራ እድል እንዲፈጥሩ ጥብቅ ክትትል አለማድረግ ችግሮች ተስተውለዋል፡፡

ተያያዥ መረጃዎች
© 2023 Lideta Subcity Job Creation. Designed by Markos Mulat G