በልደታ ክ/ከተማ "ኢትዮጲያ ታምርት" በሚል መሪ ቃል ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ምክክር ተደርጓል። በፕሮግራሙ ሪፖርት ያቀረቡት የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ጌታሁን ሀይለማሪያም እንደተናገሩት አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍና በማበረታታት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካትና ወደ ውጭም ኤክስፖርት የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ጌታሁን አክለውም በ1ኛው ኢትዮጲያ ታምርት ንቅናቄ ኢንዱስትሪዎች ሲያነሷቸው የነበሩ ችግሮችን በመቅረፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ተችሏል ሲሉ ገልፀዋል።

በልደታ ክ/ከተማ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ያመረቷቸውን ምርቶች ለእይታ በማቅረብ ማህበረሰቡ በሀገር ምርት እንዲኮራ የሚያስችል ግንዛቤ ፈጥረዋል።

ተያያዥ መረጃዎች
© 2023 Lideta Subcity Job Creation. Designed by Markos Mulat G