የልደታ ክ/ከ/ የኑሮ ውድነትና የገበያ ማረጋጋት ግብረ-ሀይል የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ፣በሬ፣በግ፣ዶሮ እና እንቁላል አቅርቦትን ማሻሻልና የመሸጫ ዋጋ ተመን ዙሪያ ተወያይቷል።

የልደታ ክ/ከተማ ም/ስራ አስፈጻሚና የስራ ፣ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሐኑ ኤኬታ እንደተናገሩት በበዓላት ወቅት የምርት እጥረት እንዳይከሰት እና የገበያ ግሽበት እንዳይፈጠር በአስሩም ወረዳዎች እቅድ አቅዶ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸው የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ከዩንየኖችና ከሸማች ማህበራት ጋር በመቀናጀት ህብረተሰቡ ያለምንም ችግር የፈለገውን ዕቃ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገበይ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

የክ/ከተማው ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ በበኩላቸው ግብረ-ሀይሉ እየሰራ ያለው ስራ ህብረተሰቡ በዓሉን ለማክበር የፈለገውን ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገበይ እንደሚጠቅመው ጠቁመው የመሸጫ ዋጋውን እና የአቅርቦት መጠን በጋራ በመወሰን የኑሮ ውድነቱን መቆጣጠር እንደሚቻል ገልጸዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በየወረዳቸው ከሚገኙ ሸማች ማህበራት ጋር በመሆን የግብርና ፣የኢንዱስትሪ ምርቶች፣ በሬ፣በግ፣ዶሮ እና የእንስሳት ተዋፅዖ የመሸጫ ዋጋ እንዲሁም የገበያ ቦታዎችን በማቅረብ የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ።

ምንጭ ፡- የልደታ ክ/ከተማ ኮሙኑኬሽን ጽ/ቤት።
ተያያዥ መረጃዎች
© 2023 Lideta Subcity Job Creation. Designed by Markos Mulat G