የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች የትንሳኤና የረመዳን በዓል ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ነዋሪዎች ማዕድ አጋርተዋል።

በማዕድ ማጋራቱ መልዕክት ያስተላለፍት የክ/ከተማው ምክትል ስራ አስፈጻሚና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሐኑ ኤኬታ እንደተናገሩት መጪውን የትንሣኤና የረመዳን በዓል ምክንያት በማድረግ የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች በራሳቸው ተነሳሽነት ከኪሳቸው በማዋጣት ማዕዱን ማጋራታቸው የአንድነት ፣የአብሮነትና የመቻቻል መገለጫ መሆኑን ጠቁመው ይህን ያስተባበሩ አካላትንም አመስግነዋል።

የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባዬ ባይሌ በበኩላቸው ሁለቱን በዓላት ምክንያት በማድረግ አመራሮች የመረዳዳትና የአብሮነት መገለጫ በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ነዋሪዎች ማዕድ አጋርተናል ብለዋል።

ምንጭ ፡- የልደታ ክ/ከተማ ኮሙኑኬሽን ጽ/ቤት።
ተያያዥ መረጃዎች
© 2023 Lideta Subcity Job Creation. Designed by Markos Mulat G